ቴራፒስቶቻችን
ሁሉም የሰለጠኑ እና የተመዘገቡ ናቸው — ስም ጠቅሰው ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ
ሕይወት አማረ
ዋና ቴራፒስት · ጥልቅ የጡንቻ ማሳጅ
በታይላንድ ቺያንግ ማይ የሠለጠነች፤ አሥር ዓመት በሙያው። የጀርባ ሕመም ላለባቸው ትመከራለች።
ለንሳ ቶሎሳ
የፊት እንክብካቤ ባለሙያ
የቆዳ ሕክምና ዲፕሎማ ያላት፤ ለአዲስ አበባ ደረቅ አየር የሚስማማ የፊት እንክብካቤ ትሠራለች።
አብዲ ሁሴን
የስፖርት ማሳጅ
ከአትሌቲክስ ክለቦች ጋር ይሠራል፤ ለሯጮች እና ለሰውነት ማጎልመሻ አባላት።
ቃልኪዳን ሙሉጌታ
የሐማም ክፍል ኃላፊ
የሞሮኮ ሐማም ሥነ ሥርዓቱን ትመራለች እና የእንፋሎት ክፍሉን ትቆጣጠራለች።
እንግዶቻችን ምን ይላሉ
ዋጋው ላይ ተጨማሪ አልመጣም። በአዲስ አበባ ስፓ ውስጥ ይህ ብቻውን ትልቅ እፎይታ ነው።
ቴራፒስቷ ግፊቱ ተስማምቶኛል ወይ ብላ ሦስት ጊዜ ጠየቀችኝ። ይሄ ሙያዊነት ነው።
ለእናቴ የስጦታ ቫውቸር ገዛሁላት። በቴሌግራም ደረሳት እና በዚያው ሳምንት ተጠቀመችበት።
ቀጠሮ በቴሌግራም
የሚፈልጉትን ሕክምና፣ ቀኑን እና ሰዓቱን ይላኩ — በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ እናረጋግጣለን። ቴራፒስት መምረጥ ከፈለጉ ስሙን ይጻፉ።