ተመሳሳይ መድኃኒት በየወሩ የምወስድ ከሆነስ?
ትዕዛዝዎን በመዝገባችን እንይዛለን፤ «ድጋሚ» ብለው ብቻ ቢልኩልን እናዘጋጃለን። ወረቀቱ ጊዜው ሲያልፍ ግን አዲስ ትዕዛዝ ያስፈልጋል።
ሁሉንም መድኃኒት ያለ ወረቀት መግዛት ይቻላል?
አይቻልም። አንቲባዮቲኮች እና ቁጥጥር የሚደረግባቸው መድኃኒቶች የሐኪም ትዕዛዝ ይጠይቃሉ — ይህ የባለስልጣኑ መመሪያ ነው።
ስለ አጠቃቀሙ ማብራሪያ ማግኘት እችላለሁ?
አዎ። ፋርማሲስቱ መጠኑን፣ ሰዓቱን እና ከምግብ ጋር ወይም ሳይኖር መወሰዱን በአማርኛ ያብራራል። ጥያቄ ካለዎት በቴሌግራምም መጠየቅ ይችላሉ።
በቴሌግራም ያናግሩን
የሚፈልጉትን መድኃኒት ወይም አገልግሎት ይላኩ — እንመልሳለን።