ተመለስ

ፋርማሲ

ተደጋጋሚ ጥያቄዎች

የሐኪም ትዕዛዜን በቴሌግራም መላክ እችላለሁ?

አዎ። የወረቀቱን ግልጽ ፎቶ ይላኩ — መኖሩን አረጋግጠን ዋጋና የሚወስደውን ጊዜ እንመልስልዎታለን። መድኃኒቱን ሲወስዱ ግን ዋናውን ወረቀት ይዘው መምጣት አለብዎት።

ወደ ቤት ታደርሳላችሁ?

በፒያሳ፣ አራት ኪሎ እና ቀጨኔ አካባቢ በ80 ብር በዚያው ቀን እናደርሳለን። ከ1,000 ብር በላይ ትዕዛዝ ማድረሻው ነፃ ነው።

የኢንሹራንስ ካርድ ትቀበላላችሁ?

ከናይል፣ ኒያላ እና አዋሽ ኢንሹራንስ ጋር ውል አለን። ካርድዎን እና የሐኪም ትዕዛዙን ይዘው ይምጡ። ለሌሎች ደግሞ ደረሰኝ እንሰጣለን።

የተጻፈልኝ መድኃኒት ከሌለ አማራጭ ትሰጣላችሁ?

ተመሳሳይ ንጥረ ነገር ያለው ጀነሪክ አማራጭ እናቀርባለን፤ ከመቀየራችን በፊት ግን ትዕዛዙን ከጻፈው ሐኪም ጋር እናረጋግጣለን።

ድጋሚ ማዘዝ

የሐኪም ትዕዛዝዎን ይላኩልን

የወረቀቱን ፎቶ በቴሌግራም ይላኩ — በ30 ደቂቃ ውስጥ መኖሩን፣ ዋጋውን እና መቼ እንደሚደርስ እንመልሳለን።

በቴሌግራም ያናግሩን

የሚፈልጉትን መድኃኒት ወይም አገልግሎት ይላኩ — እንመልሳለን።

ቴሌግራም ክፈት