ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
ተቀማጭ ገንዘብ ስንት ነው? መቼስ ይመለሳል?
የአንድ ወር ኪራይ ያህል ተቀማጭ ይያዛል። ውሉ ሲያልቅ ክፍሉ ተመርምሮ ጉዳት ካልተገኘ በ14 ቀን ውስጥ ይመለሳል፤ ተቀማጩን ለመጨረሻው ወር ኪራይ መጠቀም አይቻልም።
የወኪል ክፍያ ማን ይከፍላል?
ተከራዩ የግማሽ ወር ኪራይ አንድ ጊዜ ይከፍላል፤ ቀሪውን አከራዩ ይሸፍናል። ጉብኝት ማድረግ ግን ምንም ክፍያ የለውም።
የውሉ ጊዜ ስንት ነው?
መደበኛው ውል የአንድ ዓመት ሲሆን ኪራዩ በየሦስት ወሩ ይከፈላል። ለጌስት ሃውስ ክፍሎች ከሦስት ወር ጀምሮ ማከራየት ይቻላል፤ ማቋረጥ ከፈለጉ የሁለት ወር ማስታወቂያ ይሰጣል።
ውሃና መብራት በኪራዩ ውስጥ ናቸው?
በአብዛኞቹ አፓርታማዎች የመብራትና የውሃ ቆጣሪ የተከራዩ ነው። የጋራ ክፍሎችና የጌስት ሃውስ ክፍሎች ግን ተካተዋል። የሕንጻ አገልግሎት ክፍያ ካለ በማስታወቂያው ላይ ተለይቶ ይገለጻል።
ኪራይ ጥያቄ በቴሌግራም
የሚፈልጉትን ንብረት፣ ቀን እና ስልክ ይላኩ።