ተመለስ

ማተሚያ ቤት — ንክኪ ያለው

የአሃድ ዋጋ

እያንዳንዱ ምርት በመነሻ ዋጋው

ዋጋዎቹ ለተጠቀሰው ብዛት፣ ለመደበኛ ወረቀት እና ለሁለት ጎን ኅትመት ናቸው። ማጠናቀቂያ ከመረጡ ይጨምራል።

የብዛት ዋጋ ሠንጠረዥ
የተከመሩ የታተሙ ወረቀቶች

ፋይልዎን ይላኩ — በአንድ ሰዓት ውስጥ ዋጋ ይደርስዎታል

PDF፣ AI ወይም PSD · CMYK · 3ሚሜ ብሊድ

የንግድ ካርድ በብዛት

ብዛቱ ሲጨምር የአሃድ ዋጋው ይወርዳል — ሙሉው ሠንጠረዥ በዋጋ ገጹ ላይ አለ

  • 100 ካርድ

    650 ብርበ100

    • በአንድ ካርድ 6.50 ብር
    • በ48 ሰዓት ውስጥ
    • ማት ወይም ግሎስ ላሚኔሽን
  • 500 ካርድ

    1850 ብርበ500

    በጣም የሚታዘዘው ብዛት

    • በአንድ ካርድ 3.70 ብር
    • ነጻ የዲዛይን ማስተካከያ
    • ሁለት የወረቀት አማራጭ ናሙና
    • በአዲስ አበባ ውስጥ ነጻ ማድረስ
    ይህን ይዘዙ
  • 1,000 ካርድ

    3100 ብርበ1,000

    • በአንድ ካርድ 3.10 ብር
    • እስከ አራት ስም በአንድ ሥራ
    • በአዲስ አበባ ውስጥ ነጻ ማድረስ
  • 5,000 ካርድ

    13500 ብርበ5,000

    • በአንድ ካርድ 2.70 ብር
    • በኦፍሴት ማሽን ይታተማል
    • ወርቅ ወይም ብር ፎይል በቅናሽ

ሁሉም ዋጋ 350ግ አርት ካርድ፣ ሁለት ጎን ሙሉ ቀለም እና ማት ላሚኔሽንን ያካትታል። ተ.እ.ታ አልተጨመረም።

ከማዘዝዎ በፊት

ፋይሉን እንዴት ላዘጋጅ?

CMYK PDF፣ 300 ዲፒአይ፣ በእያንዳንዱ ጎን 3ሚሜ ብሊድ እና ጽሑፉ ከጠርዙ 5ሚሜ ወደ ውስጥ። ፊደሎቹን ወደ ቅርጽ ይለውጡ። ካልተመቸዎት ፋይሉን ላኩልን — በነጻ እናስተካክለዋለን።

ከመታተሙ በፊት ማየት እችላለሁ?

አዎ። ለሁሉም ሥራ ዲጂታል ፕሩፍ በቴሌግራም እንልካለን፤ ከ2,000 ቅጂ በላይ ለሆኑ ሥራዎች የታተመ ናሙና በነጻ እናዘጋጃለን። ሳይፈቀድ ማሽን ላይ አይወጣም።

ቀለሙ ከስክሪኑ ጋር ይመሳሰላል?

ስክሪን RGB ነው፣ ኅትመት CMYK ነው — ስለዚህ ብሩህ ሰማያዊ እና አረንጓዴ ትንሽ ይደበዝዛሉ። ትክክለኛ ቀለም ከፈለጉ የፓንቶን ቁጥር ይስጡን፤ በኦፍሴት እናዛምደዋለን።

ዛሬ ያስፈልገኛል — ይቻላል?

ለዲጂታል ሥራዎች እስከ 15:00 ካዘዙ ይቻላል፤ የችኮላ ክፍያ 25% ነው። ኦፍሴት እና ማጠናቀቂያ የሚያስፈልጋቸው ሥራዎች ግን ቢያንስ ሁለት ቀን ይወስዳሉ።

ታደርሳላችሁ?

ከ3,000 ብር በላይ ለሆኑ ትዕዛዞች በአዲስ አበባ ውስጥ በነጻ እናደርሳለን። ወደ ክልል ከተሞች በአውቶቡስ ጭነት እንልካለን፤ ወጪው በእርስዎ ነው።

ተ.እ.ታ ተካትቷል?

አልተካተተም። ሁሉም የተጻፉ ዋጋዎች ከተ.እ.ታ በፊት ናቸው። ደረሰኝ ከፈለጉ 15% ይጨመራል።

ናሙና

የናሙና መያዣውን በነጻ ይውሰዱ

አሥራ አራት ወረቀት፣ አራት ማጠናቀቂያ እና የፎይል ናሙና በአንድ ካርድ ላይ። ብቅ ብለው ይውሰዱ ወይም እናድርስልዎ።

ፋይልዎን በቴሌግራም ይላኩ

PDF፣ AI ወይም PSD ይላኩ እና የሚፈልጉትን ብዛት ይጻፉ — ዋጋና የመስጫ ቀን በአንድ ሰዓት ውስጥ ይመለስልዎታል።

ቴሌግራም ክፈት