ተመለስ

ማተሚያ ቤት — ንክኪ ያለው

አድራሻ

ልደታ፣ ከመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ጀርባ፣ አዲስ አበባ

+251 11 275 4488

ሰኞ–ዓርብ 08:00 – 18:00 · ቅዳሜ 08:00 – 14:00

በካርታ ይመልከቱ

የመቀበያ እና የመስጫ ሰዓት

ሰኞ–ዓርብ
08:00 – 18:00
ቅዳሜ
08:00 – 14:00
የዕለቱ የፋይል መቀበያ ገደብ
15:00
እሁድ
ዝግ

እስከ 15:00 የደረሰ ፋይል በዚያኑ ቀን ማሽን ላይ ይወጣል። ከዚያ በኋላ የደረሰው በማግስቱ ጠዋት ይጀምራል።

+251 11 275 4488

ከማዘዝዎ በፊት

ፋይሉን እንዴት ላዘጋጅ?

CMYK PDF፣ 300 ዲፒአይ፣ በእያንዳንዱ ጎን 3ሚሜ ብሊድ እና ጽሑፉ ከጠርዙ 5ሚሜ ወደ ውስጥ። ፊደሎቹን ወደ ቅርጽ ይለውጡ። ካልተመቸዎት ፋይሉን ላኩልን — በነጻ እናስተካክለዋለን።

ከመታተሙ በፊት ማየት እችላለሁ?

አዎ። ለሁሉም ሥራ ዲጂታል ፕሩፍ በቴሌግራም እንልካለን፤ ከ2,000 ቅጂ በላይ ለሆኑ ሥራዎች የታተመ ናሙና በነጻ እናዘጋጃለን። ሳይፈቀድ ማሽን ላይ አይወጣም።

ቀለሙ ከስክሪኑ ጋር ይመሳሰላል?

ስክሪን RGB ነው፣ ኅትመት CMYK ነው — ስለዚህ ብሩህ ሰማያዊ እና አረንጓዴ ትንሽ ይደበዝዛሉ። ትክክለኛ ቀለም ከፈለጉ የፓንቶን ቁጥር ይስጡን፤ በኦፍሴት እናዛምደዋለን።

ዛሬ ያስፈልገኛል — ይቻላል?

ለዲጂታል ሥራዎች እስከ 15:00 ካዘዙ ይቻላል፤ የችኮላ ክፍያ 25% ነው። ኦፍሴት እና ማጠናቀቂያ የሚያስፈልጋቸው ሥራዎች ግን ቢያንስ ሁለት ቀን ይወስዳሉ።

ታደርሳላችሁ?

ከ3,000 ብር በላይ ለሆኑ ትዕዛዞች በአዲስ አበባ ውስጥ በነጻ እናደርሳለን። ወደ ክልል ከተሞች በአውቶቡስ ጭነት እንልካለን፤ ወጪው በእርስዎ ነው።

ተ.እ.ታ ተካትቷል?

አልተካተተም። ሁሉም የተጻፉ ዋጋዎች ከተ.እ.ታ በፊት ናቸው። ደረሰኝ ከፈለጉ 15% ይጨመራል።

ፋይልዎን በቴሌግራም ይላኩ

PDF፣ AI ወይም PSD ይላኩ እና የሚፈልጉትን ብዛት ይጻፉ — ዋጋና የመስጫ ቀን በአንድ ሰዓት ውስጥ ይመለስልዎታል።

ቴሌግራም ክፈት