መምህራኖቻችን
ሁሉም በሕጻናት ትምህርት የሰለጠኑ እና የጤና ምርመራ ያለፉ ናቸው
ወ/ሮ ጸሐይ በቀለ
ዋና መምህርት እና መሥራች
በኮተቤ መምህራን ኮሌጅ የሕጻናት ትምህርት ተመራቂ፣ የ22 ዓመት ልምድ።
ወ/ሪት መዓዛ ሃይሉ
የመዋለ ሕጻናት ሁለት መምህርት
የንባብ ክፍለ ጊዜውን ትመራለች፤ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ታስተምራለች።
ወ/ሮ ብርቱካን ደምሴ
የሕጻናት ክፍል አሳዳጊ
ከ18 ወር እስከ 2 ዓመት ልጆችን ትከታተላለች፤ የመጀመሪያ ዕርዳታ አሠልጣኝ ናት።
አቶ ያሬድ ተክሌ
የጨዋታ እና ስፖርት መምህር
የውጪ ጨዋታውን እና የመዋኛ ክፍለ ጊዜውን ይመራል።
ወላጆች ምን ይላሉ
ልጄ ጠዋት መሄድ አልፈልግም ብሎ አያውቅም። ይህ ብቻውን ብዙ ይናገራል።
ክፍያው ግልጽ ነው። በዓመቱ መሐል ያልተጠበቀ ክፍያ አልመጣብንም።
በየቀኑ ፎቶ እና አጭር መልእክት ይላኩልናል — በሥራ ላይ ሆነን እናየዋለን።
ጉብኝት በቴሌግራም ይያዙ
የልጅዎን ዕድሜ እና የሚመችዎትን ቀን ይላኩ — ጉብኝቱ 30 ደቂቃ ነው፣ ልጅዎን ይዘው ይምጡ።