የክሊኒኩ ሰዓት
- ሰኞ–ዓርብ
- 08:30 – 19:00
- ቅዳሜ
- 08:30 – 16:00
- እሁድ
- ለሕመም ብቻ — ደውለው ይምጡ
- የማስተካከያ ቀጠሮ
- ማክሰኞ እና ሐሙስ 14:00 – 19:00
ሕመም ካለብዎት ሳይቀጥሩ ይምጡ — ሁልጊዜ አንድ ወንበር ለድንገተኛ ተይዞ አለ።
+251 11 618 2200ሰዎች ከመምጣታቸው በፊት የሚጠይቁት
ያማል?
መርፌው ከመግባቱ በፊት ድዱ ላይ የሚቀባ ማደንዘዣ ጄል እንጠቀማለን፤ ስለዚህ መርፌውን አይሰማዎትም። በሥራው መሐል ማንኛውም ጊዜ እጅዎን ካነሱ እናቆማለን።
የተነገረኝ ዋጋ ይለወጣል?
የተጻፈልዎት ዋጋ ይጸናል። በሥራው መሐል ተጨማሪ ችግር ከተገኘ እናቆምና አዲሱን ዋጋ እናሳይዎታለን፤ እርስዎ ካልፈቀዱ አንቀጥልም።
መሣሪያዎቹ የተጸዱ መሆናቸውን እንዴት አውቃለሁ?
እያንዳንዱ ስብስብ በታሸገ ከረጢት ውስጥ ሆኖ ከፊትዎ ይከፈታል። ከረጢቱ ላይ ያለው ጠቋሚ ቀለሙን ካልቀየረ አውቶክሌቭ አላለፈም ማለት ነው — እንዲያዩት እንፈልጋለን።
ማታ ላይ ጥርሴ ቢያመኝ?
ለ8890 ይደውሉ። እስከ 22:00 ድረስ ይነሳል፤ ካልተነሳ በቴሌግራም ይጻፉልን። አብዛኛው የሌሊት ሕመም እስከ ጠዋት በሕመም ማስታገሻ ይቆያል፣ የፊት እብጠት ግን ወዲያውኑ መታየት አለበት።
ልጅን ከስንት ዓመት ጀምሮ ማምጣት አለብኝ?
የመጀመሪያው ጥርስ ከወጣ በኋላ ወይም በአንድ ዓመቷ። የመጀመሪያዎቹ ጉብኝቶች መቁጠር እና ማሳየት ብቻ ናቸው — ምንም ሥራ አንሠራም።
መኪና የት አቆማለሁ?
በሕንጻው ጓሮ ስምንት ቦታ አለ። ከሞላ ከዓለም ባንክ በተቃራኒ በኩል ያለው መንገድ ላይ ማቆም ይችላሉ።
የሚያመውን ጥርስ ፎቶ ይላኩ
ፎቶውን እና ሕመሙ የጀመረበትን ቀን ይላኩ — ድንገተኛ መሆኑን ወይም እስከ ቀጠሮዎ መጠበቅ እንደሚችል እንነግርዎታለን።